ነፃ ትምህርት ዕድል ማስታወቂያ

ለትምህርት ፈላጊዎች በሰዎች ለሰዎች ድርጅት የአግሮ ቴክኒክና ቴክኖሎጂ ኮሌጅ ለ 2017 የትምህርት ዘመን የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎችን ተቀብሎ በቴክኖሎጂ መስክ በዲግሪ መርሀ ግብር ማስተማር ይፈልጋል ፡፡
በዚህ በሙያው ከፍተኛ ልምድ ባላቸው መምህራኖች እና የመማር ማስተማሩ ሂደት 70% ተግባር ተኮር በሆነው ተመራጭ ኮሌጅ ውስጥ ለመማር የምትፈልጉ፤ የ2014, 2015 እና 2016 ዓ/ም የትምህርት ሚኒስቴር የሰጠውን የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ውጤት 50% እና ከዚያ በላይ ያመጣችሁ የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች እንዲሁም በዩኒቨርሲቲ የአቅም ማሻሻያ (ሬሚዲያል) ትምህርት ወስደው ማለፊያ ውጤት (50%) እና ከዚያ በላይ ያመጣችሁ የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች የእድሉ ተጠቃሚ እንድትሆኑ ይጋብዛል ፡፡

በመሆኑም ከላይ የተጠቀሰውን መስፈርት የምታሟሉ ተማሪዎች፤

ከ ነሐሴ 13 , 2016 ቀን ጀምሮ የትምህርት ማስረጃዎቻችሁን ኮፒ ከ1 ጉርድ ፎቶ ግራፍ ጋር በመያዝ ዘወትር በስራ ሰዓት መመዝገብ የምትችሉ ሲሆን ፤ በአካል ቀርባችሁ መመዝገብ የማትችሉ በኮሌጁ ከላይ በተጠቀሱ ድህረ ገጾች በonline መመዝገብ የምትችሉ መሆኑን ያሳውቃል ፡፡ ኮሌጁ የተማሪዎችን የኮሌጅ ቆይታ ሙሉ በሙሉ የምግብ ፤ የመኝታ አገልግሎት በነጻ የሚሰጥ እና ከወጭ መጋራት ውጭ መሆኑንም ያሳውቃል ፡፡
ማሳሰቢያ ፡ በ Online ድህረ ገጻችን ላይ ለሚያመለክቱ ተማሪዎች የ12ኛ ክፍል የትምህርት ማስረጃ በሶፍት ኮፒ (በpdf) ፎርማት ለዚሁ በተዘጋጀው ፎርም ላይ መላክ ይኖርባቸዋል ፡፡

For further details and ongoing updates, please visit the ATTC dedicated information channel: https://t.me/ATTC_online
ኮሌጁ