******የነፃ ትምህርት ዕድል ማስታወቂያ ******

የነፃ ትምህርት ዕድል ማስታወቂያ

በሰዎች ለሰዎች ድርጅት ስር የሚተዳደረው የሐረር አግሮ፣ ቴክኒክና ቴክኖሎጂ ኮሌጅ ለ2014 የትምህርት ዘመን ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎችን ተቀብሎ ሙሉ ወጭያቸውን በመሸፈን በማኑፋክቸሪንግ፣ አውቶሞቲቭ፣ በኤሌክትሪካል ኤሌክትሮኒክስ ቴክኖሎጂ እንዲሁም በግብርና የትምህርት መስኮች በመጀመሪያ ዲግሪ መርሐ ግብር ማስተማር ይፈልጋል ፡፡

የመመዝገቢያ መስፈርቶች :-

1ኛ.   በ10ኛ ክፍል ብሔራዊ መልቀቂያ ፈተና በእንግሊዘኛ፣ በሂሳብ ፣ በባዮሎጂ፣ በፊዚክስ እና ኬሚስትሪ ትምህርቶች “C” እና ከዚያ በላይ ያላቸው ፤

2ኛ.   በ2013 የትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ሐገር አቀፍ ማጠቃለያ ፈተና በመጀመሪያው ዙር ተፈትነው ከ600 ድምር ውጤት የሚከተለውን  ያስመዘገቡ፤

 • ለመደበኛ ተፈታኞች
 • ወንዶች    348 እና ከዚያ በላይ
 • ሴቶች      336 እና ከዚያ በላይ ያገኙ
 • ለታዳጊ ክልልና አርብቶ አደር አካባቢዎች መደበኛ ተፈታኞች
 • ወንዶች    336 እና ከዚያ በላይ
 • ሴቶች      324 እና ከዚያ በላይ ያገኙ
 • ለግል (ድጋሚ ተፈታኞች) በሁለቱም ጾታ
 • 365 እና ከዚያ በላይ ያገኙ

3ኛ.   በ2013 የትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ሐገር አቀፍ ማጠቃለያ ፈተና በሁለተኛው ዙር ተፈትነው ከ700 ድምር ውጤት የሚከተለውን ያስመዘገቡ፤

 • ለመደበኛ ተፈታኞች
 • ወንዶች    408 እና ከዚያ በላይ
 • ሴቶች 394 እና ከዚያ በላይ ያገኙ
 • ለታዳጊ ክልልና አርብቶ አደር አከባቢዎች መደበኛ ተፈታኞች
 • ወንዶች    395 እና ከዚያ በላይ
 • ሴቶች      381 እና ከዚያ በላይ ያገኙ
 • ለግል (ድጋሚ ተፈታኞች) በሁለቱም ጾታ
 • 428 እና ከዚያ በላይ ያገኙ  

የመመዝገቢያ ቦታዎች

1ኛ.   አዲስ አበባ፦ ቦሌ ቡልቡላ በሚገኘው የሰዎች ለሰዎች ድርጅት

ዋና መ/ቤት

2ኛ.   ሐረር፣ በኮሌጁ ቅጥር ግቢ

3ኛ.   ሐዋሳ፣ በሐዋሳ ዩኒቨርሲቲ ዋናው ግቢ

4ኛ.   በተጨማሪም በድህረ ገጻችን http://www.mfmattc.edu.et online መመዝገብ ትችላላችሁ ፡፡

የምዝገባ ቀን

 • ከግንቦት 08 እስከ 10 ቀን 2014 ዓ/ም ባሉት ቀናቶች በስራ ሰዓት ብቻ ይሆናል፡፡  
 • ተመዝጋቢዎች ለምዝገባ ሲመጡ የትምህርት ማስረጃዎቻቸውን ዋናውን እና ኮፒውን እንዲሁም ማንነታቸውን የሚገልጽ መታወቂያ መያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
 • ከዚህ በፊት በመጀመሪያው ዙር መጋቢት ወር ውስጥ ተመዝግበው የነበሩት ድጋሚ መመዝገብ አይጠበቅባቸውም።
 • አመልካቾች ኮሌጁ የሚሰጠውን የመግቢያ ፈተና መውሰድ አለባቸው።

የፈተና ቦታ እና ቀን

የኮሌጁ የመግቢያ ፈተና በዚህ ማስታወቂያ የሚመዘገቡ እና በመጀመሪያው ዙር በመጋቢት ወር የተመዘገቡትን ጨምሮ መስፈርቱን በተሻለ ደረጃ ላሟሉ ግንቦት 13 ቀን 2014 ዓ/ም ከጠዋቱ 2፡30 ሰዓት ጀምሮ

 1ኛ. ሐረር በሚገኘው የኮሌጁ ቅጥር ግቢ እና

 2ኛ. አዲስ አበባ በተመረጡ መፈተኛ ጣቢያዎች የሚሰጥ ይሆናል።

ሰዎቸ ለሰዎች ድርጅት

(ሜንሽን ፍዌር ሜንሽን)