
Vacancy announcement

Agro- Technical and Technology College
የነፃ ትምህርት ዕድል ማስታወቂያ
በሰዎች ለሰዎች ድርጅት ስር የሚተዳደረው የሐረር አግሮ፣ ቴክኒክና ቴክኖሎጂ ኮሌጅ ለ2014 የትምህርት ዘመን ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎችን ተቀብሎ ሙሉ ወጭያቸውን በመሸፈን በማኑፋክቸሪንግ፣ አውቶሞቲቭ፣ በኤሌክትሪካል ኤሌክትሮኒክስ ቴክኖሎጂ እንዲሁም በግብርና የትምህርት መስኮች በመጀመሪያ ዲግሪ መርሐ ግብር ማስተማር ይፈልጋል ፡፡
የመመዝገቢያ መስፈርቶች :-
1ኛ. በ10ኛ ክፍል ብሔራዊ መልቀቂያ ፈተና በእንግሊዘኛ፣ በሂሳብ ፣ በባዮሎጂ፣ በፊዚክስ እና ኬሚስትሪ ትምህርቶች “C” እና ከዚያ በላይ ያላቸው ፤
2ኛ. በ2013 የትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ሐገር አቀፍ ማጠቃለያ ፈተና በመጀመሪያው ዙር ተፈትነው ከ600 ድምር ውጤት የሚከተለውን ያስመዘገቡ፤
3ኛ. በ2013 የትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ሐገር አቀፍ ማጠቃለያ ፈተና በሁለተኛው ዙር ተፈትነው ከ700 ድምር ውጤት የሚከተለውን ያስመዘገቡ፤
የመመዝገቢያ ቦታዎች
1ኛ. አዲስ አበባ፦ ቦሌ ቡልቡላ በሚገኘው የሰዎች ለሰዎች ድርጅት
ዋና መ/ቤት
2ኛ. ሐረር፣ በኮሌጁ ቅጥር ግቢ
3ኛ. ሐዋሳ፣ በሐዋሳ ዩኒቨርሲቲ ዋናው ግቢ
4ኛ. በተጨማሪም በድህረ ገጻችን http://www.mfmattc.edu.et online መመዝገብ ትችላላችሁ ፡፡
የምዝገባ ቀን
የፈተና ቦታ እና ቀን
የኮሌጁ የመግቢያ ፈተና በዚህ ማስታወቂያ የሚመዘገቡ እና በመጀመሪያው ዙር በመጋቢት ወር የተመዘገቡትን ጨምሮ መስፈርቱን በተሻለ ደረጃ ላሟሉ ግንቦት 13 ቀን 2014 ዓ/ም ከጠዋቱ 2፡30 ሰዓት ጀምሮ
1ኛ. ሐረር በሚገኘው የኮሌጁ ቅጥር ግቢ እና
2ኛ. አዲስ አበባ በተመረጡ መፈተኛ ጣቢያዎች የሚሰጥ ይሆናል።
ሰዎቸ ለሰዎች ድርጅት
(ሜንሽን ፍዌር ሜንሽን)