
ቀን ፡ መጋቢት 17 ፤ 2015 ዓ/ም
ማ ስ ታ ወ ቂ ያ
ለትምህርት ፈላጊዎች
በሰዎች ለሰዎች ድርጅት የአግሮ ቴክኒክና ቴክኖሎጂ ኮሌጅ ለ 2015 የትምህርት ዘመን የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎችን ተቀብሎ በቴክኖሎጂ እና በእርሻው መስክ በዲግሪ መርሀ ግብር ማስተማር ይፈልጋል ፡፡
በዚህ በሙያው ከፍተኛ ልምድ ባላቸው መምህራኖች እና የመማር ማስተማሩ ሂደት 70% ተግባር ተኮር በሆነው ተመራጭ ኮሌጅ ውስጥ ለመማር የምትፈልጉ፤ የ2014 ዓ/ም የትምህርት ሚኒስቴር የሰጠውን የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ውጤት 50% እና ከዚያ በላይ ያመጣችሁ የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች የእድሉ ተጠቃሚ እንድትሆኑ ይጋብዛል ፡፡
በመሆኑም ከላይ የተጠቀሰውን መስፈርት የምታሟሉ ተማሪዎች፤
1ኛ. ኮሌጁ ቅጥር ግቢ – Harar
2ኛ. ዋናው መ/ቤት – Addis Ababa PCO Office
ከመጋቢት 18, 2015 ቀን ጀምሮ እስከ መጋቢት 30, 2015 ድረስ የትምህርት ማስረጃዎቻችሁን ኮፒ ከ1 ጉርድ ፎቶ ግራፍ ጋር በመያዝ ዘወትር በስራ ሰዓት መመዝገብ የምትችሉ ሲሆን ፤
በአካል ቀርባችሁ መመዝገብ የማትችሉ በኮሌጁ ድህረ ገጽ http://www.mfmattc.edu.et online መመዝገብ የምትችሉ መሆኑን ያሳውቃል ፡፡
ኮሌጁ የተማሪዎችን የኮሌጅ ቆይታ ሙሉ በሙሉ የምግብ ፤ የመኝታ አገልግሎት በነጻ የሚሰጥ እና ከወጭ መጋራት ውጭ መሆኑንም ያሳውቃል ፡፡
ማሳሰቢያ ፡ በ Online ድህረ ገጻችን ላይ ለሚያመለክቱ ተማሪዎች የ10ኛ እና የ12ኛ ክፍል የትምህርት ማስረጃ በሶፍት ኮፒ (በpdf) ፎርማት ለዚሁ በተዘጋጀው ፎርም ላይ መላክ ይኖርባቸዋል ፡፡

ኮሌጁ
thank you verry much !