ነፃ ትምህርት ዕድል ማስታወቂያ

በሰዎች ለሰዎች ድርጅት ስር የሚተዳደረው የሐረር አግሮ፣ ቴክኒክና ቴክኖሎጂ ኮሌጅ ለ2016 የትምህርት ዘመን ብቁ እና ተወዳዳሪ የሆኑ የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎችን በማኑፋክቸሪንግ፣ በአውቶሞቲቭ እና በኤሌክትሪካል ኤሌክትሮኒክስ ቴክኖሎጂ የትምህርት መስኮች በመጀመሪያ ዲግሪ መርሐግብር ተቀብሎ ማስተማር ይፈልጋል ፡፡

የመመዝገቢያ መስፈርቶች :-

1ኛ.     በ2012 የትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ሐገር አቀፍ ማጠቃለያ ፈተና ተፈትነው ከ700 ድምር ውጤት የሚከተለውን ያስመዘገቡ፤

  • ለመደበኛ እና ማታ ተፈታኞች
  • ወንዶች 370 እና ከዚያ በላይ
  • ሴቶች  358 እና ከዚያ በላይ ያገኙ
  • ለታዳጊ ክልልና አርብቶ አደር አካባቢዎች መደበኛ ተፈታኞች
  • ወንዶች 358 እና ከዚያ በላይ
  • ሴቶች  348 እና ከዚያ በላይ ያገኙ
  • ለግል (ድጋሚ ተፈታኞች) በሁለቱም ጾታ
  • 375 እና ከዚያ በላይ ያገኙ
  • ለትግራይ ክልል እና መተከል ዞን
  • ወንዶች 348 እና ከዚያ በላይ
  • ሴቶች  340 እና ከዚያ በላይ ያገኙ

2ኛ.    በ2013 የትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ሐገር አቀፍ ማጠቃለያ ፈተና በመጀመሪያው ዙር ተፈትነው ከ600 ድምር ውጤት የሚከተለውን ያስመዘገቡ፤

  • ለመደበኛ ተፈታኞች
    • ወንዶች 348 እና ከዚያ በላይ
    • ሴቶች  336 እና ከዚያ በላይ ያገኙ
  • ለታዳጊ ክልልና አርብቶ አደር አካባቢዎች መደበኛ ተፈታኞች
    • ወንዶች 336 እና ከዚያ በላይ
    • ሴቶች  324 እና ከዚያ በላይ ያገኙ
  • ለግል (ድጋሚ ተፈታኞች) በሁለቱም ጾታ
  • 365 እና ከዚያ በላይ ያገኙ

3ኛ.    በ2013 የትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ሐገር አቀፍ ማጠቃለያ ፈተና በሁለተኛው ዙር ተፈትነው ከ700 ድምር ውጤት የሚከተለውን ያስመዘገቡ የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች፤

  • ለመደበኛ ተፈታኞች
    • ወንዶች 408 እና ከዚያ በላይ
    • ሴቶች 394 እና ከዚያ በላይ ያገኙ
  • ለታዳጊ ክልልና አርብቶ አደር አከባቢዎች መደበኛ ተፈታኞች
    • ወንዶች 395 እና ከዚያ በላይ
    • ሴቶች  381 እና ከዚያ በላይ ያገኙ
    • ለግል (ድጋሚ ተፈታኞች) በሁለቱም ጾታ
  • 428 እና ከዚያ በላይ ያገኙ

4ኛ.    በ2014 እና 2015 የትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ሐገር አቀፍ ማጠቃለያ ፈተና ተፈትነው ከ700 ድምር ውጤት 350(50%) እና ከዚያ በላይ ያመጡ የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች።

 5ኛ.    በ2015 ዓ/ም በዩኒቨርሲቲው የአቅም ማሻሻያ (ሬሚዲያል) ትምህርት ወስደው  ማለፊያ ውጤት (50%) እና ከዚያ በላይ ያመጣችሁ የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች።

ምዝገባ የሚያደርጉባቸው አማራጮች፦

Google form :  https://forms.gle/PRigPH6Tma9HFfPK9

Telegram Bot: https://t.me/MFMATTC_bot

በድረ ገጻችን ፡ http://www.mfmattc.edu.et መመዝገብ ትችላላችሁ ፡፡

ምዝገባ የሚያበቃው፦

  • **ጥቅምት 23/2016 ዓ.ም
  • አመልካቾች ኮሌጁ የሚሰጠውን የመግቢያ ፈተና መውሰድ አለባቸው።

የፈተና ቦታ እና ቀን

የፈተና ቀን፡

የኮሌጁን የመግቢያ ፈተና ቀን ከላይ በተገለጹት platform  እና በውስጥ ማስታወቂያ ኮሌጁ ይፋ የሚያደርግ ይሆናል፡፡ 

የፈተና ቦታ ፡

        1ኛ.     ሐረር በሚገኘው የኮሌጁ ቅጥር ግቢ እና

        2ኛ.    አዲስ አበባ በተመረጡ መፈተኛ ጣቢያዎች የሚሰጥ ይሆናል።

ማሳሰቢያ፦

  • በአቅም ማሻሻያ (ሬሚዲያል) ማለፊያ ውጤት ተመዝጋቢዎች ለመመዝገብ ውጤቱን የሚያሳይ የተረጋገጠ የትምህርት የምስክር ወረቀት ሊኖራቹ ይገባል.
  • ኮሌጁ የነፃ የትምህርት ፣ ምግብ እና ማረፊያ ይሰጠል፣ እንዲሁም  ከወጪ መጋራት (Cost sharing free) ነፃ ነው።
  • ከተመዘገቡት አመልካቾች ውስጥ ለፈተና የሚቀርቡት ስም ዝርዝራቸው ከፈተና ቦታዎች ጋር የሚገለፅ ይሆናል።

Leave a Reply

Your email address will not be published.